መሞሸርዎ ሊያሸልምዎ እና የታሪክ አካል ሊያደርግዎ ነው።
ከ1976 ዓም እስከ ዛሬዎ ቀን ድረስ በሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል የተሞሸሩ ጥንዶች እንዲመዘገቡ ጥሪ ሊቀርብ ነው።
በክብርት ወ/ሮ አማረች ዘለቀ ሽንቁጥ (እማዬ) መስራችነት በሀዋሳ ከተማ የሚገኘው የሴንትራል ሀዋሳ ሆቴል በሆቴሉ ከትንሽ ባለመደብ መቀመጫ ሆቴል እስከ ትልቅ ኮከብ ሆቴል ድረስ እጅግ ለቁጥር የሚዳግት ሙሽሮችን የሀዋሳ እናት ዋርካ የሚባሉት የነበሩት ወ/ሮ አማረች (እማዬ) ተድረዋል።
ይህንንም ትልቅ ቁጥር ያላቸው ጥንዶችን ለመመዝገብ እና ቤተሰብ ለመፍጠር; ታሪክ ለማሰናዳት; የጥንዶቹን አመታዊ ፕሮግራም ለማዘጋጀት እና ለእድለኞች ለመሸለም ዕቅድ መያዙን የእናታችን እማዬ ሁለተኛ አመት እየታሰበ ባለበት የሴንትራል ያማረች ሀዋሳ ሆቴል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት አስታውቀዋል።
ይህም ምዝገባ
1. የሰርጋቸው ቀን ወሩ; ዓመተ ምህረቱ; እና ዕለቱ
2. የሰርጋቸው 3 ፎቶ (ሆቴሉ ላይ መሆኑ የሚያረጋግጥ)
3. የመኖሩያ ሙሉ አድራሻቸው
4. የባልና የሚስት ሞባይል ስልክ ቁጥሮች
እና የመሳሰሉ መረጃዎች የሚጠይቅ የመመዝገቢያ ፕላት ፎርም በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ፍትህ ገልፀዋል
ወ/ሮ አማረች ዘለቀ (እማዬን) 2ኛ ዓመት መታሰቢያ በመንፈሳዊ; በዝክር እና በመልካመም ስራዎች ከታህሳስ 27 እስከ ጥር 12/ 2017 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ እየታሰብ እንደሚውል ተገልጿል።
www.centralyamarechhotel.com
የሆቴሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ


