banner

ቦሌ መድኃኒዓለም የሚገኘው ሳውዝ ጌት ሆቴል አፓርትመንት በአዲስ መልክ ስራ መጀመሩን አስታወቀ

#FastMereja I ከተገነባ 6 አመታትን ያስቆጠረው ሳውዝ ጌት ፕላዛ በ1.2 ሚሊየን ዶላር ተሰርቶ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ሲሆን አሁን በአዲስ መልክ ስራ መጀመሩን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል።

ሳውዝ ጌት ፕላዛ ሱቆች፣ ባርና ሬስቶራንት፣ ሁሉም ነገር የተሟላላቸው 42 ውብ የእንግዶች ማረፊያ መኝታ ክፍሎች፣ ስፓ እና የውበት ሳሎን አካቶ የያዘ መሆኑ ተገልጿል።

ሳውዝ ጌት ሆቴል አፓርትመንት ከግራውንድ እስከ 3ተኛ ፎቅ ድረስ የተለያዩ ሱቆች፣ ከ4ኛ – 9ኛ ፎቅ አፓርትመንት፣ በ10ኛ ፎሎር የሬስቶራንት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡





Leave a Comment