ባለሀብቶቹ ይህን ተከትሎ በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል
ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የተመሰረተበትን 5ኛ አመት ምክንያት በማድረግ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አድርጓል።
ይህንን በአል ምክንያት በማድረግ በበጎ ተግባሩ የሚታወቀው ወጣት ባለሀብት ምህረተአብ ሙሉጌታ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በገንዘብ እና በቁስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በሌላ በኩል የሮዳስ ቀለም ፋብሪካ እና የሮቶ አምራች ኩባንያ ስራ አስኪያጅ እና ባለቤት እንዲሁም
ሱፐር ደብል”ቲ” ሮዳስ ቀለም ባለቤት የፍኖተ ጽድቅ ጠቅላላ ማህበር መሥራችና የቦርድ ስብሳቢ አቶ ፀጋዬ ደበበ እንዲሁ ከሁለት ሚሊየን በላይ የሚገመት የገንዘብ እና የቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
በርካታ ተረጂዎችን በውስጡ የያዘው ይኸው የእርዳታ ድርጅት በበርካታ ውጣውረዶችን አሳልፎ እዚህ መድረሱን የተናገሩት ዋና ሰብሳቢዋ ወ/ሮ ሀናን መሀመድ አሁንም ህንፃዉን ለመጨረስ 1.5 ቢሊየን ብር ይቀረናል ብለዋል።
ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 4513 በተሰጠዉ ህጋዊ የሰዉነት ፍቃድ መሰረት በሴቶች የተመሰረተው ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት ላለፉት አምስት አመታት የተራቡትን በማጉርስ ፣የታረዙትን በማልበስ፣እንዲሁም ለበርካታ ወገኖቻችን የስራ ዕድል በመፍጠር በበርካታ የሰብአዊነት ተግባር ተሰማርተን የበኩሉን ሲወጣ ቆይቷል።
በዛሬው እለት ማለትም ጥር 4 ቀን 2017 አለም ባንክ በሚገኘዉ የባቡል ኸይር የምገባና የአረጋዊያን ማዕከል << እምስት አመታትን በሰብዓዊነት›› በሚል መሪ ቃል የተለያዩ የመንግስት አካላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አዘጋጅቷል




