banner

6.1 ሚሊዮን ብር ወጪ የሆነበት ጀቢና ፊልም በኔትፍሊክስ ለእይታ ሊቀርብ ነው።

#FastMereja I 6.1 ሚሊዮን ብር ወጪ የሆነበት ጀቢና ፊልም በአለም አቀፍ የፊልም እይታ በሚቀርብበት አማራጮች ለእይታ ሊቀርብ ነው። «ጀቢና» ፊልም የሚያጠነጥነው ስለአንዲት ወጣት ሲሆን ሴቷም በህይወቷ የሚደርስባትን ውጣ ውረድ እና ውጣ ውረዶቿን የምታሸንፍባቸውን ትግል የሚያሳይ ፊልም ሲሆን ከኦሮሚያ ክልል አንፃር ባህላዊ ስርአትን ማህበረሰቡ ለሴት ልጅ ያለውን አዎንታዊ አመለካከትን የምንመለከትበት ፊልም እንደሆነ ነው የተገለፀው።

ፊልሙ ሰኞ ጥር 26/2017 ዓ.ም በሐገር ፍቅር ቴአትር ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት በቀይምንጣፍ ፕሮግራም የሚመረቅ ሲሆን በእለቱ መነሻ ታሪክ ተደርጎ የተሰራበት «ምሶሶዋ» የተሰኘው መጽሐፍ ለህዝብ ይቀርባል፡፡

ከፊልሙ ምርቃት በኋላ ሀገር ውስጥ ባሉ ሲኒማ ቤቶች የማይታይ ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት ኢንተርናሽናል የፊልም ገበያዎች ጋር ለመቀላቀል እና ኢንተርናሽናል የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ለመሳተፍ አስፈላጊ ሆኖ ስተለተገኘ ከአለም አቀፍ ዲስትሪቢዩተሮች በመጣ ሀሳብ መሰረት ፊልሙ ለጊዜው ሲኒማ ቤት የማይገባ መሆኑ ተገልጿል።

ጀቢና ፊልም ዋና ተዋንያን ካሳሁን ፍስሃ (ማንዴላ)፣ ቤተልሄም ሸረፈዲን፣ እታፈራሁ መብራቱ፣ አስራት ታደሰ፣ ሉሊት ይሳቅ፣ ናትናኤል መኮንን እና ህፃን አሜን ሚኪያስ ወይም ትንሿ ኑኑ በዋናነት የተወኑበት ሲሆን ከ200 በላይ አጃቢ ተዋንያንንም ያሳተፈ ስራ ነው ደራሲ እና ዳይሬክተር ሳሙኤል ተሻገር የእማዬ ልጅ ሲሆን ኤክዝኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር ሄለን እሸቱ ፕሮዲዩሰር ቀለም ፊልምስ እና ጴጥሮስ እሸቱ፣ ፊልሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ አንድ አመት ከአንድ ወር የፈጀ ሲሆን፣ 6.1 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሆነበት ተነግሯል።

ጀቢና የአፋን ኦሮሞ ቃል ሲሆን ፅናት፣ ጥንካሬ የተሰኘ ትርጉም አለው።




6 comments

Haben Yome January 29, 2025 - 10:00 am

ተሰቃያችሁ እኮ😂‼️

Reply
Mame Galan January 29, 2025 - 10:00 am

ይሄ ሁሉ ወጪ ከየት መጣ? 🤔

Reply
Kassahun Abayneh January 29, 2025 - 10:00 am

ጁዋናም ናቹ

Reply
Enuka Kulche January 29, 2025 - 10:02 am

Camera የሚወደው ጠቅላያችን እንዳይሆን ብቻ ጀቢናዋን ሆኖ የሚተውነው😂😂🙈💪

Reply
Ashagire Shunbasha January 29, 2025 - 10:03 am

በዝህ ሰዓት እኛን የምያሳስቤን ነገር ”ጀቢና ፊልም” ሳይሆን የጀበና ቡና ዋጋ መጨመሩን ነዉ።

Reply
Sanecho Hayile January 29, 2025 - 10:04 am

ለቅሶ የለውም

Reply

Leave a Comment