ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ አርቲስቶች ስራቸውን ህዝብ ዘንድ እንዲደርስ ሰይፋ ሾ ቀዳሚ ምርጫቸው ነው ። በተለያየ የሙያ ዘርፍ ሀገርን ይጠቅማል ተብሎ የታሰበ ሁሉ ሰይፋ ሾ ላይ መቅረብ ከህዝብ ለመተዋወቅ ቀላሉ መንገድ እንደሆነ ይታመናል ፤ በአንድ ወቅት በህዝብ ዘንድ እውቅናን ያተረፋ ሰዎችና ቤተሰቦቻቸው ቢታመሙ ፣ ቢቸገሩ ከባድ የህይወት ፈተና ቢገጥማቸው እሱ ጋ ቀርበው እውቅናውን ተጠቅሞ ለብዙዎች የመፍትሄ አካል ሆኖል ። ይህ ሚዲያውን በመጠቀም ብቻ ለብዙዎች የደረሰበት ነው ።
በግሉ ለብዙዎች ብዙ ያደረገ ቢሆንም ሰው በዚህ ዙሪያ ሲያወሩበት አይወድም ፤ ቀኝ ሲሰጥ ግራ አይይ የሚል መርህ አለው ።
ለምሳሌ :— አበባ ተስፋዬ ታመው አልጋ ላይ በዋሉ ጊዜ ለ2 አመት ከሰባት ወር እየተመላለሰ የጠየቃቸውና ያስታመማቸው ሰይፋ ነው ።
ሰይፋ የሚወዳቸውን ልጆቹን እና ባለቤቱን አስፈቅዶ ለ10 ቀናት ከተወዳጅ አርቲስቶች እና ታዋቂ ሰዎች ጋር በመሆን ለመቄዶኒያ ለአረጋዊያን እና ለአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ለህንፃ ግንባት የፊኒሽንግ እቃ መግዥ እና ዘመናዊ ሆስፒታል ለተቋሙ ለማስገንባት 5 ቢሊዬን ብር በ seifu on ebs የዩቲዩብ ቻናል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በቀጥታ ስርጭት እያከናወነ ይገኛል ።
እሱ ጋር ያልቀረበ ታዋቂ አርቲስት እንዳለመኖሩ መጠን ፣ ብዙ ሀገራዊ ጉዳዬች በሱ መድረክ የመቅረባቸውን ያህል ፤ የብዙዎች ውዝግብ በእርቅ የመፍታቱን ያህል ፣ ለብዙዎች ከህመም እና ከችግር የመታደጉን ያህል ፣ ለብዙዎች የመፍትሄ አካል እንደመሆኑ መጠን ። አንድ ትልቅ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ላበረከተው አስተዋጽኦ ትልቅ የምስጋና ፕሮግራሚ ሊዘጋጅለት ይገባል የሚል እምነት አለኝ ።
via: ታሪኩ ዘውዱ




9 comments
እናመሰግናለን
አውነት መመሰገን ያለበት
ሲያሰጥ እንጂ ስሰጥ ሲመሰገን ያላየነው ሰይፉ ፋንታሁን እውነት መመስገን ያለበት ሰው ነው
ሰይፉ እራሱን ችሎ አንድ NGO ድርጅት ነው። ቀለል ያለ ሰው ስለሆነ ብዙ አልተዘመረለትም እንጅ ስንቱን ራስ ያስቻለ፣ የስንቱን እንባ ያበሰ፣ የብዙ ጀማሪ ወጣቶችን ስራ ወደ ህዝብ ያስተዋወቀ ትልቅ ሰው ነው። #እናመሰግናለን ❤️🙏❤️
Tamrat Aberaa ይህንን በደንብ አንብብ !
🤝🤝🤝🤝
እኛ ሰው ሲሞት ብቻ ነው የምናመሠግነው በቁሙ የማመስገን ባህል የለንም
ስይፎሻ❤❤❤❤🙏
ከዚህ ኘሮግራም በኃላ ይደረግለታል ብየ አስባለው አሪፍ ሃሳብ ነው፡፡