banner

ከ1500 በላይ የራይድ አሽከርካሪዎች ለአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ተዘጋጅተዋል

ራይድ ትራንስፖርት ለአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ ቀይታል፡፡ ጉባኤውን አስመልክቶ ለተመረጡ አሽከርካሪዎቹ ስልጠና ሰጥቷል፡ በስልጠናው ላይ ከ1500 በላይ የራይድ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች በንቃት ተሳትፈዋል፡፡ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ ስልጠና ለጉባዔው ከተለያዩ የአፍሪካ አገራት ለሚመጡ እንግዶች የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማጎልበት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። እንዲሁም እንግዶችን በሚኖራቸው ቆይታ መልካም ገፅታን በሚያጎላ የእንግዳ አቀባበል በማስተናገድ ደህንነታቸው እና ምቾታቸው ተጠብቆ ለመጡበት ዓላማ እንዲደርሱ ማስቻል ነው፡፡

በሥልጠናው ወቅት አሽከርካሪዎች ስለ ደንበኞች እንክብካቤ እና የእንግዶች አቀባባል ያላቸውን ግንዛቤ ለማሻሻል የሚያስችሉ የተለያዩ ልምዶችን እና ተግባራትን ሰልጥነዋል። ከተለያዩ የአህጉሪቱ አካባቢዎች ከሚመጡ አዳዲስ እንግዶች ጋር በቀላሉ ለመግባባት በሚያስችሏቸውን የስነ – ተግባቦት ክህሎት፣ የደንበኞች አቀባበል እንዲሁም እንግዶችን በመልካም መስተንግዶ መያዝን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ክህሎቶች ለማዳበር ችለዋል።

ራይድ ትራንስፖርት ከኢትዮጵያ ባሻገር በአፍሪካ ደረጃ ትኩረት በማድረግ በትራንስፖርት ኢንዱስትሪው ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን በትኩረት እየሰራ ይገኛል። ይህን ለማሳካትም ደንበኞችን ማዕከል በማድረግ ሁለንተናዊነት እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎትን፣ ከፍተኛ የአገልግሎት አፈፃፀምን፣ ታማኝነትን እና አዳዲስ እሴቶችን በማካተት በአሽከርካሪዎች እና በደንበኞች እንዲሁም በማሕበረሰቡ መካከል ያለውን መልካም መስተጋብር በማበረታታት የአገልግሎት አድማሱን የበለጠ እያሰፋ ያለ የዘርፉ አቅኝ ድርጅት ነው፡፡

አሽከርካሪዎችም በስልጠናው ያገኙት መልካም ተሞክሮ ለጉባኤው ስኬታማነት እንዲሁም ጉባኤው ከተጠናቀቀም በኋላ ዘላቂ የሆነ የደንበኞች አገልግሎት ልምድን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡ የትራፊክ መመሪያዎችን በጥብቅ በመከተል፣ የቀጠሮ ሰዓትን አክባሮ በመገኘት፣ ለእንግዶችና ደንበኞች ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት፣ እንዲሁም የእንግዶችን ፍላጎት ለማሟላት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ በሐቀኝነት ለማገልገል ቁርተኞች መሆናቸውንም አሽከርካሪዎች ተናግረዋል።

ለቀጣይ ተከታታይ ቀናት የራይድ አሽከርካሪዎች የስብሰባውን ተሳታፊ እንግዶች ከኤርፖርት፣ ከሆቴሎች እና ከተለያዩ ቦታዎች እንዲያነሱ እና እንዲያወርዱ የሚያስችላቸውን የይለፍ ባጅ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ራይድ ትራንስፖርት የአገራችንን የበለፀገ ባህልና መስተንግዶ በዓለም አቀፍ መድረኮች ጭምር በማጉላት በአሽከርካራቹ አምባሳደርነት የላቀ የደንበኞች አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል፡፡

“ራይድ” በሃይብሪድ ዲዛይንስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የተመዘገበ እና ጥበቃ የሚደረግለት የንግድ ምልክት ነው፡፡




3 comments

Farooq Al Habesha February 12, 2025 - 10:47 am

ራሳቸው ተሰብሳቢ ነውኮ የሚመስሉት

Reply
Mele Enda February 12, 2025 - 10:50 am

መቼም የአፍሪካ ተሰብሳቢዎች አይደሉም በራይድ የሚመጡት ባይሆን ቸከሶቹን የአመጣሉ

Reply
Lej Mesfin Z Tonator February 12, 2025 - 10:50 am

ገፅታ ግንባታ የትም አይደርስም መልካም ገፅታ እንጅ

Reply

Leave a Comment