0
#FastMereja I ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች በካውንስሉ በምዝገባ ቁጥር 03111 የተመዘገበች የሃይማኖት ተቋም መሆኗ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ቤተክርስቲያኒቱ የካውንስሉ አባል ስትሆን ልታከናውናቸው ከሚገቡ መመሪያዎችና ደንቦች መካከል አንዱ የካውንስሉ አባላት ስነ ምግባር መመሪያ ሲሆን በስነ ምግባር መመሪያው አንቀጽ 9.3 ላይ የስነ ምግባር ግድፈቶች ተብለው በዝርዝር የተገለጹትን ተግባራት በቤተክርስቲያኒቱ መሪ መፈጸሙን አረጋግጠናል።
በመሆኑም ጉዳዩ በካውንስሉ ሥነ መለኮት ኮሚሽን እና የሕግ ኮሚሽን ታይቶ በሚመለከታቸው አካላት የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ የቤተክርስቲያኒቱ ፈቃድ ታግዶ የሚቆይ ሲሆን ሁሉም የካውንስሉ አስተዳደራዊ መዋቅሮችና የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት ይህንንና ከዚህ በኋላ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን እንድታስፈጽሙ በግልባጭ ተመዝግቦላችኋል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል

10 comments
ካውንስሉ ሾላውን ቆረጠው 😭
ለደጋፊዎቹ መፅናናትን እንመኛለን
አሁን እውነተኛው እየሱስ ይሰበካል🙌
እንደዚህ እንደምትሆን ጠርጥሬ ነበር 🤔
የእግድን መዓት አልፎ የመጣ ሰው ነው። በዚህ ተራ ዕግድ ፈጽሞ አይሸበርም። የበሻሻው አብይ እና የሾላው ኢዩ በተራ ጫጫታ አይሸበሩም።
ኢየሱስ ከካዎንስል በላይ ነዉ።
#ደቡቦች ለተቃውሞ ሰልፍ ይወጣሉ፣ መንገድ ምናምን ይዘጋሉ፣ ቲሸርቶች ያሳትማሉ ፣ ፍቴህ ፍቴህ ይላሉ ማለት ነው? 😊
ካውንስሉ ይበተናል
ታገደ ስትል አሁን እሁድ ፕሮግራም አይኖርም ማለት ነው? አይችሉም ።
ኢዩ ጩፋ ተወገደ ሚል መስሎኝ😜😂
ለማንኛው
“እየተደነሳችሁ ሚሊየን ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንታችሁ ይገባላችኀል” ቻራ ቻራ ቱባ ሀየየየየ