banner

በነብይት ማራናታ ተክለሰንበት የተፃፈው “የታላቅ ሴት መጽሐፍ” ተመረቀ

📌 በ8 ዘርፎች እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷል

#FastMereja I ከሁለት አመት በፊት የጽድቅ ፀሐይ ለኢትዮጵያ በተሰኘ የመጀመሪያ መጽሐፍ የምትታወቀው ነብይት ማራናታ ተከለሰንበት ዛሬ መጋቢት 29/2017 ዓ.ም በሳፋየር አዲስ ሆቴል “የታላቅ ሴት መጽሐፍ” የተሰኘ ሁለተኛ መጽሐፏን አስመርቃለች።

በሁለት ቋንቋዎች በአማርኛና በእንግሊዝኛ የተፃፈው “የታላቅ ሴት መጽሐፍ” የታላቅ ሴት አለም አቀፍ ፕሮጀክት 12 ዓመታት ጉዞን እና የታላላቅ ሴቶችን ታሪክ የያዘ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ሴቶችን በማበረታታት ለቀጣይ መልካም ራዕይ አቅም የሚሆን መጽሐፍ ነው ተብሏል።

የሳቤህ ምንጭ አለም አቀፍ የወንጌል አገልግሎት ስር ባለው የታላቅ ሴት አለም አቀፍ ፕሮጀክት ባለፉት 12 ዓመታት ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖቻችን እና ድጋፍ ለሚፈልጉ የአልባሳት፣ የምግብ፣ የንጽህና መጠበቂያ ፣ የብርድልብስ፣ የፍራሽ፣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም በርካታ ድጋፎችን ለማህበረሰቡ ሲሰጥ ቆይቷል።

በታላቅ ሴት አለም አቀፍ ፕሮጀክት ስር ሴት እህቶቻችን ካለባቸው በርካታ ውስንነት ወጥተው ለራሳቸው ፣ለቤተሰብ ፣ለማህበርሰባቸው፣ ለሃገር እና በአለም አቀፍ መድረክ ጠቃሚ ዜጋ እንዲሆኑ በተለያዩ ጊዜያት የስልጠና እና የልምድ ልውውጥ ድጋፍ ሲደረግ ቆይቷል።

በዛሬው የታላቅ ሴት አለም አቀፍ ፕሮጀክት 12ኛ ዓመት ክብረ በዓል እና የታላቅ ሴት መጽሐፍ ምረቃ እለት ላይ በ8 ዘርፎች እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷል።

ነብይት ማራናታ ተክለሰንበት በአንጾኪያ የተወለዱ ሲሆን ባለትዳር እና የሁለት ልጆች እናት ናቸው። የሳቤህ ምንጭ አለም አቀፍ የወንጌል አገልግሎት ባለራእይ እና መሪ ሲሆኑ በአንድ ልብ ለትውልድ የሕፃናት፣ የሴቶች እና የአረጋዊያን መርጃ የበጎ አድራጎት ድርጅት ምስራች እና ዋና ዳይሬከተርም በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።

መጽሐፉ መታሰቢያነቱ በወንጌል ምክንያት ለተሰወኹ ለወንጌል አባቶች እና እናቶች ይሁንልኝ ብለዋል።





1 comment

Yiso Man Boom April 7, 2025 - 5:00 pm

Great👍

Reply

Leave a Comment