banner

ወተትን በጀሪካን ማከፋፈል ትክክል እንዳልሆነ ተነገረ

#FastMereja I የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከሚያከናውናቸው የቁጥጥር ሥራዎች ውስጥ የምግብ ጥራትና ደህንነት ከመቆጣጣር አንፃር በተለይም የወተት ጥራትና ደህንነት ዙሪያ በአዳማ ከተማ ለሚዲያዎች በተሰጠ ግንዛቤ ማስጨበጫ መርኀ ግብር ላይ ወተትን በጀሪካን ማከፋፈል ትክክል ያልሆነ ተግባር መሆኑን ገልጿል።

የወተት ምርት በባህሪው ጥንቃቄ የሚፈልግ በመሆኑ በተገቢው መንገድ የቅዝቃዜውን ሰንሰለት በጠበቀ መልኩ ቀዝቃዛ ፍሪጅ የተገጠመለት ታንከርና ኮንቲነር ባለበት በጥንቃቄ መጓጓዝ እንዳለበት ተገልጿል። እንደፈለጉ ውሀ በመጨመርና እንዳይበላሽ ኬሚካል እየጨመሩ ማቆየት ለከፋ የጤና እክል እንደሚዳርግ ተነግሮ ይህን ተግባር እየፈፀሙ ያሉ አካላት ከዚህ ተግባር መቆጠብ እንዳለባቸው በአፅንኦት ተነግሯል።

በተለይም ከወተት አምራቾች ወተትን በጀሪካን እየወሰዱ እንዲሁም ከቦታ ቦታ ያለበቂ ጥንቃቄ እያንቀሳቀሱ በየቤቱ የሚያከፋፍሉ አካላት ተግባራቸው ትክክል እንዳልሆነ ሊያውቁ ይገባል ተብሏል። በተጨማሪ ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ጥሬ ወተትን በጥሬው ከመጠቀም ይልቅ ፓስቸራይዝ የሆኑ ምርቶችን ቢጠቀም የተሻለ እንደሆነ ጠቁሟል።

በተያያዘ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በልዩ ትኩረት አጠቃላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የወተት አምራቾች በሙሉ የሶስትኛ ወገን የጥራት ምርመራ ሰርተፊኬትን አሟልተው ምርታቸውን ወደ ገበያ ማቅረብ እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 በተሰጠው ስልጠንና ተግባር መስረት የምግብ ጥራትና ደህንነት፣ የመድኃኒትና የህክምና መሣሪያዎች ጥራት፣ ደህንነትና ፈዋሽነትን የቁጥጥርየህክምና መሳሪያዎች ውጤታማነት የማረጋገጥ ሥራዎችን ያከናወናል፡፡

4 comments

Minab Girma May 13, 2025 - 12:04 pm

እና በእንስራ ይሁን?

Reply
BG Rooney Rooney May 13, 2025 - 12:05 pm

በብሄር ይሁን አሉ😂😂

Reply
ዮሐንስ ካሳዬ የቅዱሳኖቹ May 13, 2025 - 12:05 pm

እና በጡት ይሁን 😀😀😀

Reply
Abaynew Simegn May 13, 2025 - 12:07 pm

እንደውም በቦቲ ይሻላል

Reply

Leave a Comment