0
#FastMereja I ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ከኢትዮጵያ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚንስትር ጋር በመተባበር የዲጂታል ነዳጅ ክፍያ አማራጭ ማቅረቡን አስታወቀ።
ከዛሬ ግንቦት 06/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በተመረጡ የነዳጅ ማደያዎች በካቻ የነዳጅ ክፍያን መፈጸም እንደሚቻል የካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብርሃም ጥላሁን ተናግሯል።
አሽከርካሪዎች በካቻ አፕሊኬሽን፣ ኪውአርኮድ እና በአጭር የጽሁፍ መልዕክት በመጠቀም ክፍያ የሚፈፅሙበት አማራጭ መቅረቡን አቶ አብረሃም ገልጿል።
በቀጣይ አገልግሎቱን በመላው ሀገር ለማዳረስ እየተሰራም ይገኛል።
በተጨማሪም ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ለአሸከርካሪዎች የተለያዩ የፋይናንስ አገልግሎት አማራጮችን እያቀረበ እንደሆነ ተነግሯል።




