#FastMereja I “የድሮ አራዳ” የተሰኘው የአሌክስ ንጉስ የመጀመሪያ ሂፓፕ በአገርኛ አልበሙን ሊለቀቅ መሆኑ ዛሬ ግንቦት 5/2017 ዓ.ም በተሰጠ ጋዜጣዊ ተገለፀ።
ይህ “የድሮ አራዳ” የተሰኘው አልበም በግጥም እና ዜማ አሌክስ ንጉስ፤ ሁንአንተ ሙሉ፣ ሃብቶም፣ ደጄ ሴም የተሳተፉ ሲሆን በመዚቃ ቅንብር ፓፓ ዌዋ እና ዲናር፣ ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ 9 ትራክ ፓፓ ዌዋ እና 1 ትራክ ዲናር ተሳትፈውበታል።
“የድሮ አራዳ” አልበም 10 ሙዚቃዎች ያሉት ሲሆን አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 2 ዓመት እና 7,000,000 (ሰባት ሚሊየን) ብር በላይ መፍጀቱ በመግለጫው ላይ ተነግሯል።
አልበሙ ላይ ወይንዬ፣ ውብቂት እና ውዷ ባለቤቴ የተሰኙ ሦስት የሙዚቃ ቪዲዮዎችን ተሰርቶ የተጠናቀቁ ሲሆን ይህን ሂፓፕ በአገርኛ አልበም ሙሉ በሙሉ ወጪ በራፐር አሌክስ ንጉስ ፕሮዲዩስ ተደርጓል፡፡
ይህ “የድሮ አራዳ ሂፓፕ በአገርኛ አልበም ስለ ፍቅር፣ ስለሃገር ፣ ስለወጣት እና ስለስራ የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ይዳስሳል፡፡
ራፐር አሌክስ ንጉስ ከአሁን በፊት ወገቧን ኢትዮጵያ ትቅደም፣ ነይ ነይ፤ ለምን ብቻ እይታ በሚሉ የሂፓፕ ነጠላ ዜማዎች ለአድማጭ አድርሷል።
“የድሮ አራዳ” የተሰኘው አልበም የፊታችን አርብ ግንቦት 08 አሌክስ ንጉስ ዩቲዩብ ቻናል እና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች አማካኝነት ይለቀቃል፡፡
ሂፓፕ በኢትዮጵያ ውስጥ ከጀመሩት ውስጥ አንዱ ነኝ ሲል ራፐር አሌክስ ንጉስ በመግለጫው ላይ ተናግሯል።
#ኪነ_ጥበብ

10 comments
7 ሚሊዮን ለእሱ ሰድብ ነዉ።
ሰባት ሚሊዮን የወጣበት በባዶ ነው??
መልካም ዕድል”በግሌ አንድ አለብሽ ስባል ነው ያደኩት ብዙም ዘመናዊ ዘፈን አይገባኝም።እቅጥቅጥ ግን ኧራ አጥንትም የለኝ በድምፄስ ቢሆን መላ ጎጀም ልጁን በእኔ አይደል እዴ ይዳረው።
ሆሆሆሆሆሆሆሆ
ኧረ ና ጎበዙ ኧረ ና ጎበዙ…
ትዝታዬ😍😍😍😍
7 ሚ ብር ቢኖረኝ እኔም ሸጋ አልበም እለቅላችሁ ነበር😜😜 (ግጥም ትገዛለህ: ዜማ ትገዛለህ: ድምፅ ትገዛለህ: ቅንብር ትገዛለህ. . .)
ቱቱቱቱ አሁን ነው ጢጥ ያልየው እንደ ሀገር
የኬንያ ሽልንግ ነው
ስሙ አሌክስ አይደለም አለሙ ነዉ
እኛ ምንፈለግው የአስጌን ነው ።
ሚሊዮን ቀልድ እና ስድብ እየሆነብን ነው 🙄
ሚሊዮን አሳይሁን እስኪ ይሄ ብር ወጣበት ብቻ ምንጩ ከየት ነው 🥺🥺🥺