#FastMereja | አርቲስት ሽዋፈራሁ ደሳለኝ ሹመት አገኝቷል። ሹመቱ የአምባሳደርነት ሲሆን የኢትዬጲያ ወጣት ክርስቲያ ማህበር/E.Y.C.A ነው ሹመቱን የሰጠው።
ተቋሙ ከ20 ዓመታት በላይ የዘለቀ ሲሆን 21ኛ ዓመት የወጣቶች ምስጋና በዓል ”ታሪክ ሰሪ ትውልድ” በሚል መሪ ቃል ሊያዘጋጅ መሆኑንም በዛሬው እለት በአዶር ሆቴል በተሰጠ መግለጫ ላይ ተነግሯል።
አርቲስቱ በክብር አምባሳደርነትን ያለምንም ክፍያ በበጎ ፍቃደኝነት ለማገልገል ለ2 ዓመት የተፈራረመ ሲሆን በርካታ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ቃል ገብቷል።
የኢትዬጲያ ወጣት ክርስቲያ ማህበር/E.Y.C.A ሃምሌ5 ቀን 2017 በሚሊኒየም አዳራሽ መንፈሳዊ አገልግሎት እንደሚኖረው የገለፀ ሲሆን በርካታ ዘማሪያንና አገልጋዮች ይገኙበታል ተብሎ ይጠበቃል።
በእለቱ በሚኖረውርሀ ግብር ከ2000 በላይ ድጋፍ የሚፈልጉ ማህበረሰቦች እርዳታ የሚሰጣቸው ሲሆን ለእርዳታውም ከ4.6 ሚሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
አርቲስት ሸዋፈራሁ ይህ ጉዳይ የሁሉም ሰው በመሆኑ በከፍተኛ ችግር ያለውን ህዝባችንን መርዳት እና ትውልዳችንን በወንጌል መታደግ ስራ ላይ በገንዘብ ፣በቁሳቁስ፣ማህራዊ ሚዲያዎች ነፃ አገልግሎት በመስጠት ሁሉም በለው ነገርና አቅም ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
ብርሃን ባንክ 1601780097040
አማራጭ
ቴሌ ብር :-0912768647
ንግድ ባንክ 1000009905603 ዶ/ር





1 comment
የጌታ ሰው 🙌🙌🙌🙌
ኑሩልን እድሜ ከጤና ጋር ይስጦት 🥰🥰🫶🙄🙂