0
#FastMereja I በትግራይ ክልል የሚገኙ ውስን ስግብግብ ነጋዴዎች፣ ጦርነትና የጦርነት ወሬዎችን በመንዛት በመሠረታዊ ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በማድረግና ምርቶችን በመደበቅ በሕዝቡ ላይ እንግልትና ያልተገባ ወጪ እየፈጠሩ እንደሚገኙ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታውቋል።
መንግሥት ይህንን አስነዋሪ ተግባር በተረዱና በዚህ ድርጊት ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎችና ተባባሪዎቻቸው ላይ የማያዳግም ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ በመግለጽ፣ ነጋዴዎቹ ከዚህ ጭካኔ የተሞላበት ተግባራቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
