banner

በአሜሪካና ካናዳ የሚኖሩ የነጌሌ አርሲ ተወላጆች ለክለቡ የ35 ሚሊዮን ብር ዘመናዊ ባስ በስጦታ አበረከቱ

​#FastMereja I በአሜሪካ እና በካናዳ የሚኖሩ የነጌሌ አርሲ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ለነጌሌ አርሲ እግር ኳስ ክለብ (Negelle Arsi FC) ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ዘመናዊ የቡድን ማጓጓዣ ባስ በስጦታ ማበርከታቸው ተገለጸ።

​ይህ የተደረገው የባስ ስጦታ ክለቡ በቀጣይ የውድድር ዓመታት የሚያደርጋቸውን የጉዞ እንግልቶች በመቀነስ የተሻለ ስኬት እና ውጤት እንዲያስመዘግብ ታስቦ የተዘጋጀ ድጋፍ መሆኑ ታውቋል። ስጦታ የተበረከተው ይህ ዘመናዊ ተሽከርካሪ በአንድ ጊዜ ከ65 በላይ ሰዎችን የማጓጓዝ ከፍተኛ አቅም ያለው ሲሆን፣ የክለቡን ተጫዋቾች እና የአሰልጣኝ አባላትን ምቹ በሆነ ሁኔታ ለማንቀሳቀስ ያስችላል ተብሏል።

​የዲያስፖራው አባላት ለሀገር ቤት ክለባቸው ያደረጉት ይህ ዘመናዊ የተሽከርካሪ ድጋፍ የክለቡን የፋይናንስ እና የሎጂስቲክስ እቅስቃሴ በእጅጉ የሚያቃልል እንደሆነ ተገልጿል። ክለቡም ለተደረገለት ጥራት ያለው የትራንስፖርት ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቧል።

Leave a Comment