#FastMereja I ከሁለት ወር በታች በሆነ ጊዜ በመላ ሀገሪቱ 32 ቅርንጫፎችን በመክፈትና ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ ቁጠባ በመሰብሰብ በስፋት ወደስራ መግባቱን ዩኒቲ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ አስታወቀ። ተቋሙ በዛሬው እለት በስካይላይት ሆቴል ስራውን በይፋ መጀመሩን የሚያበስር ደማቅ ዝግጅት አከናውኗል።
የተቋሙ የቦርድ ዳይሬክተር አቶ ደመቀ አሸናፊ እንደገለጹት፤ በ38 ባለአክሲዮኖች እና በ99,900,000 ብር ካፒታል የተመሰረተው ዩኒቲ ማይክሮ ፋይናንስ ከጅምሩ አስቦ የተነሳውን ዓላማ በማሳካት ዛሬ ላይ ይህንን ስራ የመጀመሩን ብስራት እያደረገ ያለው ገና ከመሰረቱ በደማቅ ውጤትና ድል ታጅቦ ነው። በዚሁ አጭር ቀናት ውስጥ በተገኘው ስኬት አጠቃላይ የቦርድ አባላቱን፣ ማኔጅመንቱን እና ሰራተኛውን አመስግነው «እንኳን ደስ ያላችሁ» በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የዩኒቲ ማይክሮ ፋይናንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብረሃም ወዳጆ ዩኒቲ ማይክሮ ፋይናንስ ገና ከጅምሩ ራሱን በማዘመንና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው፤ ከውጭ ሀገር ያስመጣቸውን ባለሙያዎች በመጠቀም ተቋሙን ከኮር ባንኪንግ ጋር በማገናኘት በቀጥታ ስራውን እንደተቀላቀለ አስታውቀዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በፋይናንሱ ዘርፍ ትልቅ ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች ያሰባሰበው ተቋሙ፣ ያልተሰራባቸውን አዳዲስ የፋይናንስ አማራጮች ይዞ መምጣቱን በመግለጽ ለብድር ሲመጡም ያለውን ረጅም ሂደት በማስቀረት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚፈልጉትን አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ አረጋግጠዋል። ማህበረሰቡም ከጅምሩ ስኬታማ የሆነውን ማይክሮ ፋይናንስ እንዲቀላቀልና ቤተሰብ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።





1 comment
Congrat shewit