0
#FastMereja I እንደ ሱዳን ታይምስ ዘገባ፣ በሱዳን ሠራዊት (SAF) እና በሀገሪቱ ተሰማርተው በሚገኙ የትግራይ ተዋጊዎች መካከል ያለው ግንኙነት መሻከሩንና ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መግባቱን የደህንነት ምንጮች ገለጹ። በብሉ ናይል እና በኮርዶፋን ግንባሮች አጋጥመውታል የተባሉ የውጊያ ሽንፈቶችን ተከትሎ፣ የትግራይ ተዋጊዎችን ስርጭትና ጦርነት ሲያስተባብሩ የነበሩ የሱዳን ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች መታሰራቸው ለዚህ ውጥረት መባባስ ዋና ምክንያት ሆኗል።
የሱዳን ፋውንዲንግ አላይያንስ (TASIS) የተሰኘውን ኃይል ጨምሮ ከወታደራዊ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የታሰሩት መኮንኖች መታሰር ቀደም ሲል የነበረውን የምስጢርና የትብብር መስመር አቋርጦታል። በዚህም የተነሳ የትግራይ ተዋጊዎች በቦታቸው የተሾሙትን አዳዲስ አዛዦች ውድቅ በማድረግ ተጨማሪ የውጊያ ተልእኮዎችን ለመፈጸም ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ታውቋል። በብሉ ናይል ስር ባሉ አካባቢዎች በተደረገው ከባድ ውጊያ የሱዳን ሠራዊት እና አጋር ኃይሎች ማፈገፈጋቸውን ተከትሎ፣ ተዋጊዎቹ ወደ ካስላ ወታደራዊ ካምፕ አቅንተው ያለፈው ጊዜ ክፍያቸውን በመጠየቅ ወደ ግንባር ለመመለስ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

4 comments
የኬኛ ፖስት
sudan times የRSF ልሳን ነው እሺ
#ዶሮ ብታልም ጥሬዋን አለ … ቢያንስ መሻከሩ የሚለውን ቃል የሚተካ ብትፈልጉ 🤔😂
ትርጉም በ ስለሺ😂