0
የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት የ2016 ዓ.ም በጀት አመት የሁለተኛ እቅድ አፈፃፀም እና የ2017 ዓ.ም በጀት እቅድን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በዛሬው እለት ሰጥቷል።
በ2010 ዓ.ም ተግባራዊ የተደረገው የታሪፍ ማስተካከያ ከ 12 ዓመት በኃላ መደረጉ የተነሳ ሲሆን በዚህም በተቋሙ የተጀመሩ ስራዎች ብድር ባለመክፈላቸው እና ተቋሙ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ለማካሄድ ችግር ውስጥ በመሆኑ የፍጆታ ታሪፍ ሂሳብ ማሻሻያው ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ ሊያደረግ መሆኑን በመግለጫው ተገልጿል፡፡
የታራፍ ማሻሻያ ክፍያው በሰኔ 13 2016ዓ.ም በኢነርጂ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ማሻሻያ መፅደቁን ይታወሳል ።
በዚህም ማሻሻያ ክፍያው በቤት ደንበኞች ታሪፍ በዝቅተኛው 50 ኪሎ ዋት ተጠቃሚ ላይ በ አንድ ኪሎዋት ከ27 ሳንቲም ወደ 35 ሳንቲም መደረጉን እና ከ4 ዓመት በኋላ በጠቅላላ ድምሩ በ አንድ ኪሎ ዋት 6 ብር ጭማሪ እንሚመጣ ይህም ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት አስታውቋል ሲል ጄሬዲዮ ነው የዘገበው።

10 comments
የ አየር (የምንተነፍሰውን) መቼ ነው የምታስከፍሉን እንዘጋጅ!!!
ደሞዙስ🤔🤔
እረ በጣም ደስ ይላል አባይ ግድቡ ማመንጨት ስለጀመረ ታሪፉን ልትቀንሱልን ነው ሺ አመት ንገሱ
ቢሆንም ድል ለግብጽ አልልም 😎
ማሻሻያው ለመስርያቤቱ ነው ለህብረተሰቡ ጭማሪ ሊደረግ ነው ነው የሚባለው ማሻሻያ ማለት ጥሩ ያልሆነ ነገር ጥሩ ለማድረግ ሲታሰብ ነው ለመስርያቤቱ ግን እርግጥ ነው ማሻሻያ ነው ይሁን ምን እንላለን!!
አሳስቦን ነበር
አማሩን
ደሞ ለዚህ መብራት የምን ጭማሪ ነው ዝናብ ሲመጣ ፈርቶ ለሚጠለል
በዚህም በዚያም እያላቹ ህዝቡን ለማሳበድ ነው አላማቹ
አባይ ለጎረቤት ሀገር ነው የተሠራው?