0
#FastMereja
የቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስፖርት ጋዜጠኛ የነበረው ዮናስ ሀ/መስቀል ያዘጋጀው ፊልም ለዕይታ ሊበቃ መሆኑ ታውቋል:: ከኢትዮጵያ ወጥቶ ኑሮውን በካናዳ ያደረገው የቀድሞ የስፖርት ጋዜጠኛ ዮናስ ሀ/መስቀል በድርሰት እና ዝግጅት ተሳትፎ ያደረገበትን “ቃላት” የተሰኘውን የበኩር ፊልሙን ዛሬ መስከረም 8/2024 እ.ኤ.አ ኑሮውን ባደረገበት ቶሮንቶ ለኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ አባላት ለእይታ እንደሚያበቃ ለኤፍ ኤም አዲስ ገልጿል።
ከምረቃ በኋላ በሚኖረው መረሃ ግብር ወደተለያዩ የካናዳ ከተሞች ለኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ አባላት እንደሚታይ የገለፀው ዮናስ በቀጣይ ፊልሙን ወደ ኢትዮጵያ ይዞ የመምጣት ዕቅድ እንዳለው አንስቷል።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስፖርት ጋዜጠኛ ዮናስ ሀ/መስቀል ለስምንት ያክል ዓመታት በሙያው የሰራ ሲሆን ከሀገር ከወጣ ስምንት ዓመታት እንዳስቆጠሩ በቆይታው አንስቷል።
ከአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በቲያትር ጥበባት የመጀመሪያ ድግሪውን ያገኘው ዮናስ ሀ/መስቀል ወደ ካናዳ ካቀና በኋላ የፊልም ትምህርቱን ሊከታተል መቻሉን ገልጿል።

10 comments
ይቻላል እንደ😁
የሚያበላውን ነው የመረጠው
የሚያዋጣውን እሱ ያቃል
ለምን ወደ እርሻ ስራ ኣይገባም🧐
ወይ እምየ አሜሪካ አሁን ይኼን ዮናስ ነው ብየ ልመን እረ እኔንም ጥሪኝ 🤔
ዘፈንም እደሞከረ አስታውሳለሁ
Tadiya egna mn ageban, weregna😜
በዚሁ አጋጣሚ ዮናስ ኃ/መስቀል ሙዚቃም እንደሞከረ ለማስታወስ እወዳለው። ካልተሳሳትኩ 2003 ዓ.ም አካባቢ አንድ ነጠላ ዜማ ለቆ በዚያው ጠፋ 🫣🫣🫣🫣
Good luck
Good luck 🤞 Yonisha😉