banner

ሐዋሳ የሚገኘው የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦትና አገልግሎት መድኃኒት በድሮን ለማድረስ ሙከራ አደረገ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦትና አገልግሎት ሐዋሳ ቅርንጫፍ አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ በማዘመን ኢመርጀንሲ የሆኑ እና አንዳንድ የመንገድ ችግር በሚስተዋልበት ወቅት ለጤና ተቋማት ክትባቶችን ማድረስ የሚያስችል የድሮን አገልግሎት ሙከራ በተሳካ ሁኔታ እያደረገ ይገኛል።

ድሮኗ በዋናነት ክትባቶችን የምታጓጉዝ ሲሆን ከ15 ደቂቃ ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በተፈለገው ስፍራ አድርሳ ትመለሳለች። በቀጣይ ከፍተኛ ክብደት ያለው በርካታ ክትባቶችን የሚያደርስ ድሮን ለማቅረብም በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ለዚህ ትልቅ ተግባር የሚተጉ የድርጅት መስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊዎችና የሐዋሳ ከተማ መድኃኒት አቅርቦትና አገልግሎት ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመን ለገሰ ሊመሰገኑ ይገባል።

Via: ኤፍሬም




1 comment

Oniv Brezzy December 11, 2024 - 9:53 am

ኢትዮጵያ ግን ቅብጥጥጥ አለች 😭😁

Reply

Leave a Comment