banner

በአዲስ አበባ አሮጌ መኪናዎች የኮሪደር መንገዶች እንዳይንቀሳቀሱ ክልከላ ሊደረግባቸው ይችላል ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ፥ የአሮጌ መኪና ባለቤቶች መኪናቸውን በፍጥነት መቀየር ካልቻሉ በለሙ የኮሊደር መንገዶች ላይ እንዳይንቀሳቀሱ ክልከላ ሊደረግባቸው ይችላል ብለዋል።

አሮጌ መኪናዎች የአገልግሎት ዕድሜ ገደብ ፀድቆ ወደስራ ሊገባ ይገባል ያሉት ኃላፊው አሁን አግልግሎት እየሰጡ ያሉ የአሮጌ መኪና ባለቤቶች ፈጥነው መቀየር እንዳለባቸው እንደተገለጸላቸው ተናግረዋል።
መኪናዎቹ በካርቦን ልቀት፤ በትራፊክ መጨናነቅና በተገልጋዮች ምቾት አለመስጠት እንቅፋት እየሆኑ ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከተሽከርካሪ ባለንብረቶችና ከአስመጪዎች ጋር በመሆን የብድር አገልግሎት እንዲያገኙና መኪኖች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ድጋፍ እንደሚሰጥ ሰምተናል ሲል አራዳ ሬዲዮ ነው የዘገበው።

10 comments

ነጭ ወርቅ December 26, 2024 - 7:47 pm

አሮጊት እና ሽማግሌስ😂

Reply
Bili Teshe December 26, 2024 - 7:47 pm

ሌላ የትችት እርስ
ፈርዶበታል መንግስት 😋😊

Reply
Melaku Mekonen December 26, 2024 - 7:48 pm

አለባበስ አይተዉ ብቻ መንገድ እንዳያስቀይሩን

Reply
ፍቅር ፍቅር December 26, 2024 - 7:51 pm

ገና በሙሉ ልብስ ካልዘነጣቹ ከቤት እንዳትወጡ እንባለለን 🙄 አይ ፀሀዩ መንግስታችን 😏 ተደበሩብን

Reply
Aminu Shafi December 26, 2024 - 7:51 pm

ብቻ አካል ጉዳተኞን ከቤት እንዳትወጡ እንዳይባል 😢

Reply
Hanny Konjo December 26, 2024 - 7:53 pm

የትኛው አለም ላይ ነው ሰውዬው የሚኖረው ከህልሙ ተነስቶ እንዲህ መጫወቻ ያድርገን አይ እማማ ኢትዮጵያ😏😏😏

Reply
የብሄር ነጋደው December 26, 2024 - 7:54 pm

ገና ህዝቡም እንደሚያግዱት ይጠበቃል

Reply
Habib Ozz December 26, 2024 - 7:54 pm

እውነት ለመናገር እኔ የምኖረው ከሀገር ውጪ ነው የ 1990 እንዲሁም ከዛ በታች ያሉ መኪናዎች እራሱ ይነዳሉ ስለዚህ ቢታሰብበት መልካም ነው

Reply
Gebrela Hope December 26, 2024 - 7:54 pm

እድሜ ይስጠን እንጂ ገና ብዙ …………….

Reply
Dawit Ilma Abbaa Raammatte December 26, 2024 - 7:54 pm

ላዳ ጉድሽ ፈላ ! 🤣

Reply

Leave a Comment