0
“ስሜን ለማጥፋት ነው” ዲጄ ቤቢ
#FastMereja I የአርቲስት ዓለማየሁ ደመቀን የ25 ዓመታት የኪነጥበብ ቆይታና አገልግሎት ለማክበርና አርቲስቱን ለማመስገን ዮቶር በሚል ርዕስ ሰኔ 15/2016 ዓ.ም የሙዚቃ ኮንሰርት በማርዮት ሆቴል አዳራሽ መከናወኑ ይታወቃል፡፡
በዝግጅቱ የተገኙ ገቢዎች የስፖንሰርሺፕ ገቢ፣ የቲኬት ገቢና ሌሎችም ገቢዎች ሂሳብ ተሰርቶ ርክክብ ባለመደረጉ በተደጋጋሚ ሂሳብ ተሰርቶ የአርቲስቱ ድርሻ ገቢ እንዲደረግለት ጥያቄ ቢቀርብም በተለያዩ ምክንያቶች ዲጄ ቤቢ መገኘት ባለመቻሉ ጉዳዩ እልባት ማግኘት አልቻለም ሲሉ ኮሚቴዎቹ ቅሬታውን በደብዳቤ ለሚዲያዎች ገልፀው ነበር።
ጉዳዩን አስመልክቶ ፋስት መረጃ ዲጄ ቤቢን አነጋግሮ የሚከተለውን ምላሽ አግኝቷል ደብዳቤው ቀድሞ ተልኮልኝ አይቼዋለሁ ያለው ዲጄ ቤቢ እንደአጋጣሚ ሆኖ አሜሪካን ሀገር በላስ ቬጋስ ከተማ በተዘጋጀው የአለም የሬዲዮና ቴሌቪዥን ብሮድካስተሮች ማህበር ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ አሜሪካ ሀገር ሄጃለሁ እሱን አጋጣሚ በመጠቀም “ሸሸ” በማለት ስም ለማጥፋት የተደረገ ስም የማጥፋት ዘመቻ ነው፣ ሙሉ በሙሉ ውሸት ነው! ጉዳዩን ወደ ህግ ወስጄዋለሁ ብሏል።
#ሾውቢዝ

4 comments
ጉዳዩ ሀገር ጥሎ የመሸሽ አይደለም 👉የሰበሰብከውን የሰው ገንዘብ አስረክብ ነው እንጂ 😃😃😃✔️ክፈል!!!
አሁን ጥያቄው የዚህን መልካም ሰውን ገንዘብ ትመልሳለህ አትመልስም?
እሺ አልሸሸህም እንበል ግን ብሩን ትከፍላለህ አትከፍልም🙄
ለ #Baby ገንዘብ ያዠ ይደረጋል?? ትልቅ ሰው ጠፍቶ ነው 😃