banner

የትምባሆ ምርቶች ማራኪ ሆነው መቅረባቸው ወጣቶችን እያሳሳቱ ነው ተባለ።

#FastMereja I የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም የሚከበረውን የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀንን ምክንያት በማድረግ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ለማስጨበጥ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ38ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ33ኛ ጊዜ ዘንድሮ ግንቦት 23/2017 ዓ.ም የሚከበረውን ትምባሆ የማይጨስበት ቀን የዓለም ጤና ድርጅት በትምባሆ እና በኒኮቲን ምርቶች ላይ የትምባሆ እንዱስትሪ አሳሳችና ድብቅ ስልቶችን በማጋለጥ ወጣቶችን እንታደግ በሚል መሪ ቃል እንዲከበር የወሰነ ሲሆን ዘመቻው የትምባሆ እና የኒኮቲን ኢንዱስትሪዎች ጎጂ ምርቶቻቸውን ማራኪ ለማስመስል የሚጠቀሙባቸውን ዘዴዎች በማጋለጥ ላይ እንዲያተኩር ተደርጓል ተብሏል።

የዘንድሮው የዘመቻ ርዕስ የተመረጠበት ዋነኛ ምክንያት በአሁን ወቅት ካሉት ግንባር ቀደም የህብረተሰብ ጤና ችግሮች መካከል በተለይም ለወጣቶች ጤና ተግዳሮቶች ከሆኑት ውስጥ ትምባሆ፣ ኒኮቲን እና ተዛማጅ ምርቶችን ማራኪነት/ሳቢነት ባላቸው መንገድ መቅረባቸው ሲሆን የትምባሆ ኢንዱስትሪው እነዚህን ምርቶች አጓጊ ለማድረግ ሽታቸው ጣዕማቸው ወይም መልካቸውን የሚቀይሩ ቅመሞችን እና ሌሎች ንጥረ ነሮችን በመጨመር ያለማቋረጥ ሙከራዎች በማድረግ የትምባሆ ምርቶች ጉዳት ለመደበቅ ጥረት በማድረግ ላይ በመሆኑ ነው::

በአሁኑ ወቅት ዘመናዊ ምርቶችን ለመጠቀም እንደ ቁጥር አንድ ምክንያት ሆነው ይጠቀሳሉ፡፡ በመሆኑም እነዚህ የትምባሆ ኢንዱስትሪዎች ጎጂ የሆኑ የትምባሆ ምርቶችን እና ሱስ የሚያስይዙ የኒኮቲን ምርቶቻቸውን በመጠቀም በተለይም ለወጣቶች ማራኪ እንዲሆኑ በማድረግ ስውር ስልቶችን ይጠቀማሉ ተብሏል።

ከሚጠቀሙባቸው ስልቶች መካክል ማራኪ ግብይት፣ ቄንጠኛ ዲዛይኖች ማራኪ ቀለሞች እና ማራኪ ጣዕሞች በዲጂታል ሚዲያ ቻናሎችን ጨምሮ ወጣቱን የህብረተሰብ ክፍል ለመሳብ ስልታዊ በሆነ መንገድ ተጠቅመው ገበያ ላይ ያውላሉ። በተጨማሪም አሳሳች ንድፎች፣ ማቀዝቀዣች እና ተጨማሪ ማጣፈጫዎችን እንደሚጠቀሙ ተገልጿል።

ስለሆነም ይህን የትምባሆ ኢንዱስትሪዎች ጣልቃገብነትና ድብቅ ሴራ ለማጋለጥ የዘንድሮ በዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን መሪ ሀሳብና ጭብጥ በመጠቀም የህብረተሰቡን ግንዛቤን ማሳደግ ወሳኝ ተግባር ተደርጎ መወሰድ አለበት ተብሏል።

2 comments

ፍቅር ያሸንፋል May 28, 2025 - 9:51 am

እንደ አቢቹ መልኩ አምሮ ነው የፎገረን 😄😄
@highlight

Reply
Nur Ahmed May 28, 2025 - 9:52 am

እንኳን ትምባሆ ሴቶች ጭምር መንገድ ላይ አሳሳች ሆንዋል አዲስ በመጣው የዳሌ ፕላስቲክ

Reply

Leave a Comment