#FastMereja I በጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ የተጀመረው የሸገር ገበታ ኢኒሼቲቭ የአዲስ አበባ ኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ማሳካቱን የአዲስ አበባ ከተማ የከተማ ውበት እና የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ግርማ ሰይፉ ገለፁ።
የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ከተማውን አረንጓዴ ለማድረግ የታቀደውን 30%, ወደ 22% ማሳካቱን ጠቁመዋል።
የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ንፁህ አየር መተንፈስ ፣ ውብ አካባቢ መኖር ፣ የሥራ እድል የፈጠረ ፣ የቦታ ዲሞክራሲ የሰጠ መሆኑን የገለፁት አቶ ግርማ በኮሪደር ልማት ምክንያት ተፈናቀለ የሚባለው ድህነት እንጂ ደሀ አይደለም ብለዋል።
በየኮሪደሩ ዙሪያ የተሰሩት የልጆች መጫወቻ ምን ያህል ለትውልድ እንደታሠበ አመላካችና የትውልድን ራዕይ ያሳካ ነው ብለዋል።
የተሠራው የኮሪደር ልማት የከተማውን 15% የሚሸፍን ቢሆንም በጋራ በራስ አቅም የማልማት ሂደቱ ይቀጥላል ብለዋል።
የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ወጤታማነት የገባቸው የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላት ለወከሉት ህዝብ መቼ ወደ እኛ ጋር ይደርሳል የሚል ጥያቄ መመለስ ስለሚገባ የተጀመረውን የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ቅድሚያ መጨረስ ይገባል ብለዋል።
Via: OBN

6 comments
አቤት ጭንቅላት
ይሄን ብላ
OBN ከዘገበው ልክ ነው 😀
ዋው አስተሳስብ ብሎ ዝም።
ግርማ ግርግር🙊
ኢትዮጵያ በነዚህ ነው የምትመራው