0
#FastMereja I የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ ዳግም ዛቻ መሰንዘራቸውን ተከትሎ፣ የኢራን መንግስት “ፈጣን እና ጠንካራ የአጸፋ እርምጃ” እንደሚወስድ በማሳሰብ አስገራሚ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን የኑክሌር መርሃ-ግብር እና በቀጠናው ያላትን ተጽዕኖ ለመግታት “ከባድ እርምጃ” ሊወስዱ እንደሚችሉ በድጋሚ ገልጸዋል። ይህም ዋይት ሃውስ በኢራን ላይ የነበረውን “ከፍተኛ ጫና የማሳደር” ፖሊሲ በይፋ መመለሱን ያሳያል ተብሏል።
የኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣናት አሜሪካ ለምትሰነዝረው ለማንኛውም ጥቃት ወይም ወታደራዊ ትንኮሳ በደቂቃዎች ውስጥ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል። “ለማንኛውም አይነት ስህተት ዋጋ እናስከፍላለን” ሲሉ መሪዎቹ ዝተዋል።
ይህ የቃላት ጦርነት በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ እና በሌሎች ወሳኝ የንግድ መስመሮች ላይ የጸጥታ ስጋት ደቅኗል። ዓለም አቀፍ ተንታኞች ሁኔታው ወደ ቀጥታ ወታደራዊ ግጭት እንዳያመራ ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
