#FastMereja I በሜክሲኮ እጅግ አደገኛ እና ጨካኝ የሚባለው የጃሊስኮ አዲስ ትውልድ ካርቴል መሪ ኔሜሲዮ ኤል ሜንቾ ኦሴጌራ ሰርቫንቴስ፣ የካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም በሜክሲኮ ጦር ሃይል በተፈጸመ ድንገተኛ ወረራ ተገደለ።
ወታደራዊ ወረራው የተካሄደው በጃሊስኮ ግዛት፣ ታፓልፓ በተባለች ስፍራ ነው። ኤል ሜንቾ በጸጥታ ኃይሎች እና በታጣቂዎቹ መካከል በነበረው ከባድ የተኩስ ልውውጥ ቆስሎ ለህክምና ወደ ሜክሲኮ ሲቲ በመወሰድ ላይ ሳለ ሕይወቱ አልፏል።
ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል የ15 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አውጥቶ የነበረው የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ለዘመቻው ስኬት ትልቅ ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል።
በአሁኑ ሰዓት ማህበራዊ ሚዲያውን እያናወጠው ያለው ጉዳይ የኤል ሜንቾን መደበቂያ ቦታ አሳልፎ የሰጠው አካል ማንነት ነው። እንደ Telemundo ዘገባ እና በኤክስ ላይ እየተሰራጩ ባሉ መረጃዎች መሠረት
ማርያ ጁሊሳ የተባለችው ዝነኛ የOnlyFans ሞዴል እና የኤል ሜንቾ የፍቅር አጋር፣ መደበቂያ ቦታውን ለጸጥታ ኃይሎች አሳልፋ ሰጥታለች ተብሏል።
ይህ የክህደት ወሬ በካርቴሉ አባላት ዘንድ ከፍተኛ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፣ ሞዴሏም ለኤል ሜንቾ መጨረሻ ምክንያት ሆናለች እየተባለ ይገኛል።
የኤል ሜንቾን መገደል ተከትሎ በሜክሲኮ ከተሞች ላለፉት ዓመታት ታይቶ የማይታወቅ እጅግ የከፋ የኃይል እርምጃ እና የግጭት ማዕበል ተቀስቅሷል። የካርቴሉ ታጣቂዎች መንገዶችን በመዝጋት እና ተሽከርካሪዎችን በማቃጠል በጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት እየሰነዘሩ ይገኛሉ።
የኤል ሜንቾ ካርቴል በጭካኔው ስለሚታወቅ ሞዴሏ ላይ የበቀል እርምጃ ሊወስድ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አለ። ዜናው ከተሰራጨ በኋላ ሞዴሏ ከማህበራዊ ሚዲያ ገጾቿ መራቋ እና የት እንዳለች አለመታወቁ ወሬውን ይበልጥ እንዲጋጋል አድርጎታል።
