0
#FastMereja I ተፈቅደው ጥቅም ላይ የሚውሉ የፕላስቲክ ማሸጊያዎች በአዋጁ መሠረት የሚከተሉትን ምርቶች ለማሸግ የሚውሉ ፕላስቲኮች የተፈቀዱ መሆናቸውን ባለሥልጣኑ አስታውቋል፡-
📌 ለምግብ ምርቶች፡ እንደ አትክልትና ፍራፍሬ ያሉ የጥሬ ምግቦች መጠቅለያዎች።
📌 ለባልትና ውጤቶች፡ የተለያዩ የባልትና ውጤቶችን ለማሸግ የሚያገለግሉ ፕላስቲኮች።
📌 ለልብስ ማጠቢያ (Laundry) አገልግሎት፡ የታጠቡ ልብሶችን ከብክለት ለመጠበቅ የሚውሉ ቀጭን ፕላስቲኮች።
📌 ለሌሎች የፋብሪካ ምርቶች፡ ምርቱን ከፋብሪካ እስከ ተጠቃሚ ድረስ በጥራት ለማድረስ የሚያገለግሉ ማሸጊያዎች።
ምንም እንኳን እነዚህ ማሸጊያዎች የተፈቀዱ ቢሆንም፣ አጠቃቀማቸውና የቆሻሻ አወጋገዳቸው በአዋጁና አዋጁን ተከትለው በሚወጡ አስፈጻሚ ሕጎች መሠረት መሆን እንዳለበት በጥብቅ ታዟል። ይህም ፕላስቲኮቹ በአካባቢ ላይ የሚያደርሱትን ብክለት ለመቀነስ ታስቦ የተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
