0
#FastMereja I በቅርቡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ባለውለታና ግዙፍ ስም ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ “ሊፈርስ ነው” በሚል ሲሰራጭ የነበረውን መረጃ ተከትሎ፣ ታዋቂው ድምጻዊ ያሬድ ነጉ ለክለቡ ያለውን ጥልቅ ፍቅርና አጋርነት ገለጸ።
ድምጻዊው ባስተላለፈው መልዕክት፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከክለብነት ባለፈ የአገር ኩራትና የታሪክ ተምሳሌት መሆኑን አውስተዋል። ያሬድ በመልዕክቱ ክለቡ አሁን ያለበትን ፈታኝ ወቅት በጽናት እንዲያልፍ የሞራል ድጋፍ እንደሚሰጥና “ንቅንቅ የለም” በማለት ጥንካሬውን ገልጿል።
ቅዱስ ጊዮርጊስና ቡና ገበያ የአዲስ አበባ ድምቀትና የኢትዮጵያ ብራንዶች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ክለቡ የማይነካ የአገር ቅርስ መሆኑን አረጋግጧል።
”ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ አገር ገናና ትልቅ ባለታሪክ ክለብ ነው” ያለው ድምጻዊው፣ የክለቡ መዳከም ለጠቅላላው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ውድቀት መሆኑን አስገንዝቧል።
”ይህ ጊዜ አልፎ እናያለን፤ ክፉ አይንካችሁ” ብሏል።
