banner

በትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የሚዲያ አጠቃቀም ላይ የታየው ለውጥ

​#FastMereja I የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የማህበራዊ ሚዲያ ገጽ ከቀናት በፊት የክልሉን ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ መግለጫዎች ሲያጋራ ቆይቶ፣ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን “የክልሉ ፕሬዝዳንት” በማለት ዘገባዎችን ማቅረብ ጀምሯል።

​ይህ በጽሕፈት ቤቱ ይፋዊ የመረጃ መረብ ላይ የታየው ለውጥ በክልሉ ያለውን ከፍተኛ የፖለቲካ አመራር ሚና እና ተዋረድ በተመለከተ አዲስ አቅጣጫ መጠቆሙ ተመልክቷል። ላለፉት ጥቂት ቀናት የጽሕፈት ቤቱ ገጽ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ በሚሰጡ መግለጫዎች እና በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ነበር። ሆኖም ዛሬ የወጡ ዘገባዎች ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን በፕሬዝዳንትነት ማዕረግ በመጥቀስ የቀረቡ ሲሆን፣ ይህም በክልሉ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ትልቅ ትኩረት የሳበ ክስተት ሆኗል።

Leave a Comment