banner

በጋምቤላ 190 የጂን አልኮል መጠጥ እንዲወገድ ተደረገ

#FastMereja I ​በጋምቤላ ክልል አኙዋሃ ብሔረሰብ ዞን አቦቦ ወረዳ ውስጥ የተከለከለ የአልኮል መጠጥ ይዘው በሚዘዋወሩ ግለሰቦች ላይ ፖሊስ ባደረገው ጥብቅ ክትትል 190 የጂን አልኮል መጠጦችን በቁጥጥር ሥር አውሎ እንዲወገዱ ማድረጉን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

​የአቦቦ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ አቶ አሮፖ ኡበንግ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፣ ሕገ-ወጥ የአልኮል መጠጦችን በሚያዘዋውሩ ግለሰቦች ላይ ወረዳው ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግና አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።

​አክለውም የተከለከሉ የአልኮል መጠጦች በማኅበረሰቡ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትሉ በመሆናቸው፣ ኅብረተሰቡ ይህንን ሕገ-ወጥ ተግባር የሚያከናውኑ ግለሰቦች ሲያጋጥሙት በአፋጣኝ ለወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ጥቆማ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ አዛዡ ጥሪ አቅርበዋል።

4 comments

Dewota Kass November 25, 2026 - 11:36 am

ወይ ፈብሪካዉን መዝጋት ከድሀ ላይ ከምትደፉ የተረገመች ሀገር

Reply
Bertaw Gesese November 25, 2026 - 11:38 am

እኔ መጠጣት ባቆምኩበት ወቅት በመሆኑ ነው እንጅ በጣም ያናድዳል

Reply
እዮብ መኮንን November 25, 2026 - 11:39 am

ብሄራዊ አረቄ ፋብሪካ እኮ የመንግስት ነው እንዴት ቢዳፈሩ ነው መንግስት ያመረተውን ምርት የሚደፉት

Reply
Biruk Buna November 25, 2026 - 11:39 am

Zemua Buna 😭

Reply

Leave a Comment