የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ሚኒ-ባሶች፣ ሚዲ-ባስ ታክሲዎችና የከተማ አውቶብሶች ላይ የአገልግሎት ታሪፍ ጭማሪ ማድረጉ ይታወሳል ፡፡
ይህንኑ በተመለከተ አስተያየታቸውን ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን የተናገሩ ነዋሪዎች የተደረገው የትራንስፖርት ታሪፍ ጭማሪ የተጋነነ ነው ብለዋል ። አስተያየታቸውን ከሰጡት ነዋሪዎች መካከል አንድ በባንክ ስራ ተቀጥሮ የሚሰራ ግለሰብ ከመኖሪያ ቤቱ እስከ ስራ ቦታው ድረስ በደርሶ መልስ ከ100 ብር በላይ እንደሚያወጣ ተናግሯል ።
ይህ ማለት ደግሞ በወር ውስጥ በስራ ገበታዬ 26 ቀናት ስገኝ ከ2600 ብር በላይ ይሆናል ብሏል ። በተመሳሳይ ሌሎችም አስተያየታቸውን ለጣቢያችን የተናገሩ ነዋሪዎች በቀን ለትራንስፖርት የሚያወጡት ገንዘብ ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል ።
ምንም እንኳን የትራንስፖርት ጭማሪው የተደረገ በአዲስ አበባ ከተማ ቢሆንም ሸገር ከተማን ጨምሮ ከተለያዩ አካባቢዎች መኖሪያቸው በማድረግ የስራ ቦታቸው አዲስ አበባ የሆኑ ነዋሪዎች በአጠቃላይ ለትራንስፖርት የሚያወጡት ገንዘብ ከፍተኛ መሆኑን ይናገራሉ ።
ለአብነትም አንድ አስተያየት ሰጪ ከመኖሪያዬ ተነስቼ የቀጠረኝ ድርጅት የሚገኝበት አካባቢ ለመድረስ ለደርሶ መልስ 150 ብር ወጪ አደርጋለሁ ይላሉ ። ሆኖም በህዝብ ትራንስፖርት ላይ የተደረገው የታሪፍ ጭማሪ የተጋነነ ነው የሚሉት ነዋሪዎች ጭማሪ ቢደረግ እንኳን በዚህ ልክ መጋነኑ ተገቢ አይደለም ብለዋል ።
አዲሱ የታሪፍ ጭማሪ ከጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ጭማሪ በተደረገበት በአዲሱ ታሪፍ ዝቅተኛው 10 ብር ሲሆን ከፍተኛው 65 ብር ነዉ።
Via: ዳጉ ጆርናል

10 comments
ወደሽ ከተደፋሽ አይክፋሽ …
አንድ ክልል ብቻውን እታገለ ነው እንጅ መንግስት ጣሉኝ እያለ ነው ታገል ለነፃነትህ
ዝቅተኛው 5 ብር ነው ጭማሬው🤔
ሚገርመው ነገር እኮ መንግስት ይፋ ሳያደርገውም እየከፈልን አልነበር እንዴ ?
እና ይጨመር ?
የባሴ አይምጣብን ይሄንን ኑሮ የሆነ ጊዜ ይናፍቀን ይሆናል
ገዚህም ካልጨመረ ተመስገን ማለት ነው
ቀጥሎ ደግሞ ከታክሲዎች ላይ ገንዘብ መሰብሰብ የሚያስችል አዲስ ህግ ይፀድቃል ።
እጅ አዙር ማለት ይሄ ነው ‼️
yebelew yehe hizeb tenituwal gena mene ayeto …
65 ብር ክፍለ ሃገር ነው?🙄