#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ እና ኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ጋር በመተባበር HOME COMING ADDIS በሚል መሪ ቃል የዳንስ ፊትነስ የካቲት 2/2017 ዓም በዓድዋ ሙዚየም እንደሚካሄድ ዛሬ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
ፕሮግራሙ የከተማው ነዋሪዎች እና ከውጭ ሀገር ትውልደ ኢትዮጵያን እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
የዳንስ ፊትነስ በከተማችን መዘጋጀቱ ባህላዊውን ውዝዋዜ ከዘመናዊው ዳንስ ጋር በማዋሐድ የሚዘጋጅ በመሆኑ ለአገር ገጽታ ግንባታ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የማህበረሰብ ስፖርት ማስፋፊያና ማደራጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንግዳወርቅ ዳንኤል ገልፀዋል።
የኢትዮ ዳንሰ ፊትነስ አሰልጣኝ እና መስራች ቶማስ ኃይሉ በበኩላቸው በፕሮግራሙ ከ10ሺ በላይ ሰዎች ለማሳተፍ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ይህ ከተሳካ በዳንስ ፊትነስ በአፍሪካ ደረጃ ቀዳሚ እንደሚሆን አሳውቀዋል።
የካቲት 2 ቀን 2017 ከ10:00 ሰዓት እስከ ምሽት 3:00 ሰዓት በአድዋ ድል መታሰቢያ የሚካሄድ መሆኑ በመግለጫው ተገልጿል።
ቲሸርቱን ከኢትዮ ዳንስ ፊትነስ ጂም ያገኙታል፣ የመግቢያ ዋጋ በነፃ ሲሆን በኢትዮ ዳንስ ፊትነስ መመዝገብ ያስፈልጋል።





3 comments
ፐ ችግር ፈቺ አይደል!
መሪ ቃሉ ሸገር ትደንሳለች ቢሆንስ🤗🤗😂😂😂😏
ፓ ውሃው ላይ ፎቶ የሚነሱት አራዶች ሊወዛወዙ ነዋ 😁