#FastMereja I በአሁኑ ወቅት በህክምና ላይ የሚገኙት ታዋቂው የማህበራዊ ሚዲያ በጎ ፣ድራጊ ማስተር አብነት ከበደን ስም በመጠቀም፣ የተሳሳቱ መረጃዎችና የማጭበርበር ድርጊቶች እየተፈጸሙ መሆኑ ተገለጸ። ማስተር አብነት ለፋስት መረጃ በላከው ልዩ መግለጫ፣ ህዝብ ከእነዚህ መሰል ድርጊቶች ራሱን እንዲጠብቅ አሳስቧል።
የማጭበርበር ሙከራዎችና የAI ቴክኖሎጂ ስጋት
ማስተር አብነት በህክምና ላይ መሆኑን ተገን በማድረግ፣ በተለያዩ የሀሰት (Fake) አካውንቶች እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ተቀናብረው የሚወጡ ምስሎች፣ ጽሁፎችና ተንቀሳቃሽ ምስሎች በስፋት እየተሰራጩ መሆኑ ተረጋግጧል።
ከዚህም ባለፈ አጭበርባሪዎች በውስጥ መስመር (Inbox) የድምጽና የጽሁፍ መልዕክቶችን በመላክ፣ “ለህክምና ድጋፍ” በሚል ስም የደጋግ ሰዎችን ገንዘብ ለመዝረፍ ሙከራ እያደረጉ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።
መግለጫው በግልጽ እንደሚያስረዳው፦
📌 ለማስተር አብነት ከበደ ህክምና የሚውል ምንም ዓይነት የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ አይደለም።
📌 በማንኛውም መንገድ በስሙ የሚጠየቅ የገንዘብ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ ሀሰተኛ እና ለማጭበርበር የታለመ ነው።
በማስተር አብነት ስም የተከፈቱ በርካታ የሀሰት ገጾች ቢኖሩም፣ ተከታዮች መረጃ እንዲቀበሉ የተፈቀደላቸው በሚከተሉት ትክክለኛ ገጾቹ ብቻ መሆኑ ታውቋል፦
Facebook: ከ1.9 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ገጽ።
TikTok: ከ5.7 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ገጽ።
በመጨረሻም፣ ህዝባችን እና የሚዲያ ተከታዮች ካልተረጋገጡና ከተቀናበሩ የሀሰት መረጃዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ፣ እንዲሁም መረጃዎችን ከታመኑ ምንጮች ብቻ እንዲከታተሉ ጥብቅ መልዕክት ተላልፏል።





1 comment
If so which one is real?