የሮድሪ የውድድር ዘመን አብቅቷል ፔፕ ጓርዲዮላ አረጋግጧል::
በዚህ ሳምንት በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማን.ሲቲ ያለ ሮድሪ ከኒውካስል ጠንካራ ግጥሚያ ይጠብቀዋል::
የሊጉ መሪ ማን.ሲቲ ከሜዳው ውጪ ኒውካስልን በሚገጥምበት ጨዋታ የሮድሪን መልክ እና ቅርፅ የያዘ ጉድለት/ክፍተት በአማካይ ክፍሉ ይኖረዋል:: ይህ ጨዋታ ገና በጊዜ ስፔናዊዉን ማጣት ያለፉትን የውድድር ዘመናት የዋንጫ አሸናፊ ቡድን ደካማ ጎን ሊያሳይ ይችላል::
የ28 ዓመቱ አማካይ የቀኝ ጉልበቱ ጅማት ጉዳት ደርሶበታል በተጋጋለው እና ሁለት አቻ በተጠናቀቀው ማን.ሲቲ ኤቲሃድ ላይ አርሰናልን ባስተናገደበት ጨዋታ:: ሮድሪ አስቀድሞ አስታውቋል አስጠንቅቋል ተጫዋቾች በጨዋታ መደራረብ ምክንያት አቅም እንደሚያጡ በአካልም በአእምሮም እንደሚዝሉና ጉዳት እንደሚያስተናግዱ:: በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ለሲቲ እና ስፔን ብ.ቡድን 63 ጨዋታዎችን አድርጓል::
የጉዳቱ ክብደት ሲቲ ተጫዋቹን ለረጅም ጊዜያት እንደማያገኘው ያስረዳ ነበር:: የቡድኑ አለቃ ፔፕ ጓርዲዮላ ለችግሩ መፍትሔ መፈለግ አለበት::
የቁጥር መረጃ ጥናቱ እንደሚያሳየው የጓርዲዮላው ቡድን ሲቲ ሮድሪን ሲይዝ ቡድኑ የበለጠ ከፍ ያለ ብቃት ላይ ይገኛል ለመርታትም አዳጋች ይሆናል::
ያለፈው የውድድር ዘመን ሶስቱም ሽንፈቶቹ (የሲቲ) የተመዘገቡት ያለ ሮድሪ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ነበር:: ሮድሪ በ 2019 ከአትሌቲኮ ማድሪድ ሲቲን ከተቀላቀለ ጀምሮ ቡድኑ ከ 21 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ሮድሪን ባላሰለፈባቸው 7 ጨዋታዎች ተሸንፏል:: የመሸነፍ መጠን 33%
ከሮድሪ ጋር (በቡድን ሲኖር/ሲሰለፍ) 174 ጨዋታዎች 4 ተከታታይ የፕ.ሊግ ሻምፕዮን የመሸነፍ መጠን 10.9%
ጓርዲዮላ ሲገልፀው የማይተካ ይለዋል ነገር ግን ለችግሩ መፍትሔ መፈልግን “የእኔ ግዴታ” ነው ይለዋል::
“በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ሶስት ወራትን ያለ ኣርሊንግ ሃላንድ አምስት ወራትን ያለ ኬቨን ደ ብሩይነ አሳልፈናል እናም መፍትሔ ሰጥተነዋል/ አግኝተንለታል::”
ሮድሪ በሚያደርገው/በሚሰራው ነገር በዓለም እግር ኳስ ከእሱ የተሻለ የለም የሚባልለት ነው:: ስለዚህ ለረጅም ጊዜያት እርሱን በጉዳት ማጣት ለሲቲ ቀላል አይሆንም:: ማን.ሲቲ በሚያደርገው የዋንጫ ፉክክር ላይ እና ለአምስተኛ ተከታታይ ጊዜ ክብሩን ለማግኘት በሚኖረው ተስፋ ላይም ተጽዕኖ እንደሚኖረው መገመት ይቻላል::
ከኒውካስል ጋር በሚኖረው ጨዋታ የሲቲ የትኛውም ስህተት/ ሸርተት ማለት ሊቨርፑል አስተን ቪላ አርሰናል ቼልሲን ጭምር በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ አቀማመጣቸውን ከፍ ያደርገዋል:: (እንደየጨዋታዎቹ ውጤት) ሊቨርፑል ዎልቭስን ይገጥማል አርሰናል ሌስተር ሲቲን ያስተናግዳል::
10 ነጥቦች የያዘው ቼልሲ በያዘው አቋም እና በሚያበረታታ ውጤቱ ለመቀጠል እያሰበ ሰባተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ብራይተንን በሜዳው ያስተናግዳል::
ማን.ዩናይትድ ከቶተንሃም በኦልድ ትራፎርድ እሁድ 12:30
የእግር ኳስ ቤተሰቦች የእናንተስ ሃሳብ? 👇
[ ሰላም ጎሳዬ ለፋስት መረጃ ከአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ]

9 comments
Mak Chelsea
ድል ለ አርሰናል💪
የኛ ሐሳብማ
አጥሚቱን እና አጃውን
በምን እንላክለት ነው 😂
ድል ለ አርሰናል ብለናል😀💪
Manchester City yashenifal tsufun ye tsafew ye arsenal degaf new
ዋንጫውን ማንሳቱ አይቀርም🔵
አያሳስባቹ…Here is the solution on the hand of Pep and Citizinans💙
ይህ አመት ማን ሲቲ ፕሪመርሊግና ቻምፒዮንስሊግ አይወስድም ያለ ሮድሪ አይታሰብም። ለማንኛውም ሰኔ 2017 መጀመርያ ሳምንት ላይ እንገናኝ
We are citizen 💙