banner

ንብረትነቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት ኃይል አገልግሎት የሆነ የመንገድ መብራት ምሰሶ ለመቁረጥ ሲመክሩ የተያዙ ተከ

ንብረትነቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት ኃይል አገልግሎት የሆነ የመንገድ መብራት ምሰሶ ለመቁረጥ ሲመክሩ የተያዙ ተከሳሾችን በፅኑ እስራት ማስቀጣቱን የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

ተከሳሾች አስራት የሱፍ እና ፍቃዱ አለቃ ሲባሉ ወንጀሉን የፈፀሙት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አቧሬ ጭንጫ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው፤ ተከሳሾቹ ጨለማን ተገን በማድረግ ንብረትነቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት ሀይል አገልግሎት የመንገድ መብራት ምሰሶ የብረት መቁረጫ መጋዝ ወይም ሴጌቶ በመያዝ ለመቁረጥ ሲሞክሩ በአካባቢው የነበረ የጥበቃ ሰራተኛ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ አማካኝነት ተከሳሾቹ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አምስተኛ ወንጀል ችሎት እንደተሳፏቸው መጠን በተከሳሽ አስራት የሱፍ ላይ በ6ዓመት ከ6ወር እንዲሁም በተከሳሽ ፍቃዱ አለቃ ላይ ደግሞ 1ዓመት ከ6ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በህዝብና በመንግስት ሀብት ላይ የሚፈፀሙ ማናቸውንም የወንጀሎች አይነቶች በመከላከል እና በመቆጣጠር ረገድ ህብረተሰቡ እያደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትና ጥቆማ በመስጠትም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡


10 comments

Etsana Tesfay February 12, 2025 - 10:40 am

ኢ/ያ እንኳን ከ ጨለማ ዘመን ወደ ብርሃን ዘመን አሸጋገረሽ 🤣

Reply
እውነት/Truth February 12, 2025 - 10:45 am

ሀገሪቱን የማፍረስ ድርሻ የባለስለጣን ብቻ ማን አደርገው ብለው ነው😄

Reply
Wubetu century metal works February 12, 2025 - 10:46 am

ከስራ ወደ እስር ቤት መልካም የእረፍት ዘመን 😁

Reply
Yodit Yo February 12, 2025 - 10:46 am

ሻማ ነጋዴ ልከዋቸው ይሆን 🙄

Reply
Abusha Arsenal February 12, 2025 - 10:49 am

ሲርበው ምን ያድርግ😭

Reply
የመከራዋ ምድር ምድር ማን ነች February 12, 2025 - 10:53 am

ጨለማን ተገን በማድረግ ስትሉ ፖሉ ፓውዛ የለውም ማለት ነው ከሌላው ጥቅሙ ምንድነው ሽጠው ይጠቀሙ እንጂ 😂😂

Reply
Natinael Samuel February 12, 2025 - 10:55 am

የማንያዘዋል ንግግር ከሰማህ በኋላ 😂😂😂😂

Reply
Åbđī Ťëšfŷę February 12, 2025 - 10:57 am

በዝህ ድፍረት እኮ ነዉ ጣልያንን የተዋጋነዉ🤝 ይፈታልን😭

Reply
Ayele Gizaw Gemechu February 12, 2025 - 11:00 am

ጨለማን ተገን አድርጎ?ቀን አይደለም ፎቶው

Reply
Ethio Robel Calisthenics February 12, 2025 - 11:37 am

First of all if it’s both them are the culprit why sentence difference? Second of all the verdict is unfair and seems that have no one to defend them so please if anyone reading this comment who is a lawyer should speak for them (do some pro Bono )🙏

Reply

Leave a Comment