banner

በአንዱዓለም ጎሳ እና በቀነኒ ቤተሰቦች መካከል የተጀመረው የዕርቅ ሂደት ተቋረጠ

#FastMereja I ​በወጣት ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረውና በኋላም በዋስ የተፈታው ድምጻዊ አንዱዓለም ጎሳ፣ ጉዳዩ በኦሮሞ ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት (በአባ ገዳዎች) እንዲያልቅ ጥረት ሲደረግ ቢቆይም ሂደቱ ሳይሳካ መቅረቱ ተገለጸ።

​የዕርቁ መቋረጥ ዋና ምክንያቶች፡-
📌 ​የቤተሰብ ቅሬታ፡- የሟች ቀነኒ አባት አቶ አዱኛ ዋቆ፣ ድምጻዊው በዋስ መፈታቱ እንዳሳዘናቸው ገልጸው፣ “የልጄን ደምም ሆነ እውነት እስካሁን አላገኘንም” ብለዋል።

📌 ​የሥርዓቱ አካሄድ፡- የአባ ገዳዎች ስብሰባ (ጋዲሳ) ለሦስት ጊዜያት የተካሄደ ቢሆንም፣ በአራተኛው ቀጠሮ ላይ የሟች አባት ሳይገኙ ቀርተዋል። አባ ገዳ ጎበና ሆላ እንደገለጹት፣ ቤተሰቡ ለዕርቁ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሂደቱ ተቋርጧል።

📌 ​የእውነት ፍለጋ ልዩነት፡- አቶ አዱኛ “ገዳዮች ሳይለዩና ድርጊቱ ሳይታመን ‘ጉማ’ (የደም ካሳ) አንቀበልም” በሚል ሂደቱን ተችተዋል። አንዱዓለም በበኩሉ ድርጊቱን እንዳልፈጸመውና እውነቱ እንዲወጣ እንደሚፈልግ ለአባ ገዳዎቹ ሲገልጽ ቆይቷል።

ቤተሰቦቿ ቀናኒ በሰው እጅ እንደተገደለች ሲያምኑ፣ አንዱዓለም ግን ራሷን እንዳጠፋች በመግለጽ መከራከሩ በሁለቱ ወገኖች መካከል መግባባት እንዳይፈጠር አድርጓል።

4 comments

Shimelis Eshetu December 31, 2025 - 12:03 pm

የምን እርቅ ነዉ የሰዉ ነፍስ እኮ ነዉ የጠፋዉ ትክክለኛዉን ፍርድ መፍረድ ነዉ ወንጀለኛዉን በህግ መቅጣት አከተመ።

Reply
Kumarraa lammi December 31, 2025 - 12:03 pm

😎😎

Reply
Mehaliy Solomon December 31, 2025 - 12:04 pm

እዚህ ላይ ነው እንግዲህ የጠቢቡ ሰሎሞን ዳኝነት የሚያስፈልገው

Reply
ማኅደር የሺወንድ December 31, 2025 - 12:05 pm

ጀግና አባት በልጁ ደም ገንዘብ አይቀበልም!!!!

Reply

Leave a Comment